የሳይበር ደህንነት ለስማርት ሲቲ በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀዉ ሲንፖዚየም ላይ ፖናል ዲስከሽን ተካሄደ

by Communication Office


Posted on 2016-12-24


የሳይበር ደህንነት ለስማርት ሲቲ በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀዉ ሲንፖዚየም ላይ ፖናል ዲስከሽን ተካሄደ

 

ITDB፦ ታህሳስ 4/2017 ዓ.ም

የሳይበር ደህንነት ለስማርት ሲቲ በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀዉ ሲንፖዚየም ላይ ከተለያዩ ተቋማት የተወጣጡ ፖናሊስቶች ማለትም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ምህረቱ ደሳለኝ፣ ቡራዮ ታለንትድ እና ጊፋትድ አካዳሚ ዳይሬክር አቶ መሳይ ሀይለማርያም፣ የኢንሳ ኢንፎርሜሽን ኔትወርክ ደህንነት አድምንስትሬሽን መረጃ ደህንነት አቶ ሀኒባል ለማና የኢትዮጵያ ሳይበር ሰኪዮሪቲ አሶሴሽን ፕሬዘዳንት ዶ/ር ብርሃኑ በየነ የተለያዩ ሀሳቦች የተነሱ ሲሆን ከተነሱ ሀሳቦች መካከል፦

- ከሳይበር ደህንነት ግንዛቤ ከመስጠት አንፃር እንዲሁም የ8 ዓመት ስማርት ሲቲ ስትራቴጂ ትግበራ ዕዉን ለማድረግና ሳይበር ሰኪዉሪቲ ስጋት ለማስወገድ የኢኖቬሽንና ቴእኖሎጂ ልማት ቢሮ ምን እየሰራ እንደሆነ

- ዲጅታል 2025 ዕዉን ከማድረግ አንፃር የሳይበር ደህንነት ለማስጠበቅ ምን እየተሰራ ነዉ

- የሳይበር ደህንነት አሶሴሽን የሳይበር ደህንነት ስጋት ለመቀነስ ዘላቂነት ያለዉ ግንዛቤ ማስጨበጫ ከመስጠት አንፃር ምን እየሰራ እንደሚገነኛና ዉጤቶቹ

- የሳይበር ደህንነት ስጋት ለመቀነስ ኢንሳ ምን አይነት የቁጥጥር ስራ እየሰራ መሆኑን ለሚሉ ጥያቄዎት ፓናሊስቶች ዝርዝር ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ከተሳታፊዎች የተነሱ ሀሳብ አስተያየቶችን እንደግብአት በመዉሰድ ዉይይቱ ተጠናቋል።

በመጨረሻም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ ሰለሞን አማረ ከተማችን ከምስራቅ አፋሪካ የተሻለች እንድትሆን የስማርት ሲቲ ሰነድን መነሻ በማድረግ ከተማ አስተዳደሩ ከተለያዮ ተቋማት ጋር እየሰራ መሆኑንና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ በከተማዉ ያሉ የመንግስት ተቋማት ዲጅታል እንዲሆኑ የበኩሉን አስተዋፅኦ እያበረከተ መሆኑንና ከዚህም ባሻገር 11ዱ ክ/ከተሞችና ወረዳዎች በሲቲ ኔት እያስተሳሰረ እንደሚገኝ ገልፀዋል። አያይዘዉም አምስት ሚሊዮን ኢትዮ ኮደርስ ማፋራት ዋና አላማዉ ዲጅታል ኢትዮጵያን ዕዉን ማድረግ መሆኑን በማመላከት ፕሮግራሙ ለታደሙ አካላት ምስጋናቸዉን አቅርበዋል።

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB

ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et

መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714


Leave a Comment:


Good News 2024-12-16

Good News

News Search

Resently News

Resently News .