የኮደርስ ስልጠና

by ITDB


Posted on 2019-03-25


የኮደርስ ስልጠና

በተያዘው ዓመት 75 ሺህ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የኮደርስ ስልጠና እንዲወስዱ እየተሰራ ነው

AMN - መጋቢት 10/2017 ዓ.ም

በተያዘው በጀት ዓመት 75 ሺህ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የኮደርስ ስልጠና እንዲወስዱ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰለሞን አማረ ከኤኤም ኤን ውሎ አዲስ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደተናገሩት፤ በአዲስ አበባ በ 3 አመታት ውስጥ 3 መቶ ሺህ ዜጎችን የቴክኖሎጂ እውቀት ባለቤት ለማድረግ እየተሰራ ነው፡፡

በተያዘው በጀት ዓመት ብቻ 75 ሺህ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የኮደርስ ስልጠና ይወስዳሉ ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል፡፡

በኢትዮ ኮደርስ ፕሮግራም ላይ አራት የስልጠና አይነቶች መኖራቸውን የገለጹት ኃላፊው ፕሮግራሙ ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ ባለፉት 7 ወራት እንደሃገር ከ550 ሺህ በላይ ዜጎች በስልጠናው እየተሳተፉ መሆናቸውን አስታውሰዋል፡፡ በአዲስ አበባም 160 ሺህ ዜጎች በስልጠናው እየተሳተፉ መሆናቸውን ተናግረዋል ፡፡

በስልጠናው ተሳትፈው ሰርተፍኬት የያዙ ግለሰቦች ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር እራሳቸውን በማላመድ ውጤታማ መሆናቸውን የገለጹት ኃላፊው በተለይም በመንግስት ተቋማት ውስጥ የሚገኙ ሰራተኞች ስልጠናውን ቢያገኙ አገልግሎት አሰጣጣቸውን ማሳደግ እንደሚችሉ ጠቁመዋል፡፡

ስልጠናው እንደ አዲስ አበባ በትምህርት ቢሮ ፤ በሲቪል ምዝገባና ነዋሪዎች አገልግሎት እና በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች እየተሰጠ በመሆኑ ይህን ዕድል ሁሉም ዜጋ ሊጠቀም እንደሚገባ የአዲስ አበባ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰለሞን አማረ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

#ITDB


Leave a Comment:


Dfff 2025-03-26

Cgff

News Search

Resently News

Resently News .