by Gulelle Communication Office
Posted on 2026-03-25
የአገልግሎት ቀንን ለተገልጋይ ብቻ !! "
አስተዳደሩ የአገልግሎት ቀንን ለተገልጋይ ብቻ የሚለውን አቋም ይዞ በአገልጋይነት መንፈስ ህዝቡን በግልፅነት ማገልገል ከጀመረ ሰነባብቷል።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የአንድ ማዕከል አገልግሎት ረቡዕና ዓርብን ማዕከል አድርጎ ከክፍለ ከተማ ባሉ በሁሉም ጽህፈት ቤቶች እየተሰጠ ሲሆን ለተገልጋይ ክብር ሲባል የደንበኛ መረጃ መስጫ ማዕከላትንም ማደራጀት ተችሏል። በዚህም በርካታ የመልካም አስተዳደር ችግሮች እየተፈቱ ይገኛል።
በዛሬው ዕለትም በሁሉም ጽ/ቤቶች የተገልገይን ዕለት ለተገልጋይ ብቻ በማዋል ተገልጋዩን ህብረተሰብ በክብር ፣ በቅንነት በታማኝነትና ውጤታማ በሆነ አሰራር እያገለገለ ውሏል።
በአገልግሎት አሰጣጡ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ ፣የጉለሌ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚና ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ታደሰ እና ሴክተር መስሪያ ቤቶች አንድ ዓይነት ጉዳይ ያላቸውን በጋራ ምላሽ በመስጠት፣ ወረፋን በመጠበቅ የሚጠፋ ጊዜን በመቆጠብ፣ ብልሹ አሰራርን ለማስወገድና ግልፀኝነትን በመፍጠር በልዩ ትኩረት እየተሠራ ነው።